በአረንጓዴ አየር ንብረት ፈንድ (Green Climate Fund) ፕሮጀክት በድሬዳዋ እና በሀረር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች አበረታች መሆናቸን የፕሮጀክቱ የሴክሬተሪያት ቡድን አባላት ገለፁ::
የአረንጓዴ አየር ንብረት ፈንድ (Green Climate Fund) ፕሮጀክት የሴክሬተሪያት ቡድን አባላት በድሬዳዋ እና በሀረር በፕሮጀክቱ የተሰሩ ስራዎችን በመጎብኘት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱም የእርስ በእርስ ግንኙነቱን በሚያጠናክሩ እና ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ በሚገኝበት ሀሳቦች ዙሪያ መክረዋል። በውይይት መድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና፣ ዉሃ፣ መአድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ በመስክ በፕሮጀክቱ ከንፁህ መጠጥ…


