የዲፕሎማሲያችን ማጠንጠኛው ብሔራዊ ጥቅም እና የዜጎች ክብር ነው፦ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ
ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀ ሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የዲፕሎማሲያችን መሰረታዊ ማዕከል እና ማጠንጠኛው ብሔራዊ ጥቅም እና የዜጎች ክብር ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በመደርጀት ላይ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህ ስትራቴጂያዊ ምርጫ ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ተላሚነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለመሸጋገር አስችሎናል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪ ሀብቶቿ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ስትቀበል፤ በዛው…


