አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ለግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ፍትሀዊ የግብር አሰባሰብ ሂደትን እንዲፈጠር በማድረግ በኩል ጉልህ ሚና እንዳላው ተገለጸ
የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በተሻሻለው የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ላይ በአስተዳደሩ ለሚገኙ ለንግዱ ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል። ውይይቱ በዋናነት የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በተለይም የግብር ስርዓቱ ላይ የሚታዩ የፍትሀዊነት ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት የወጡ አዋጆችን ለንግዱ ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ አላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል። በውይይት መድረኩም…


