“ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞቹን ከህልማቸው በማገናኝት ከድህነት ወደ ብልጽግና እያሸጋገረ ያለ ተቋም ነዉ ” ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የማህበረሰቡን የጋራ እድገትን እውቅና የሚሰጥበት ዓመታዊ የደንበኞች ኮንፍረንስ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል። በመርሃ ግብሩም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በአስተዳደሩ ኢኮኖሚ ላይ እያሳደረ ያለውን በጎ ተጽእኖ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው በዚህም ስራ ፈጣሪ ወጣቶች፣ ሴቶች ፣ነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች እና የእጅ ባለሞያዎች በመደበኛ ብድር የማግኝት እድል…


