የምስራቅ ሀረርጌን ሠላም ለማስመለስ የወጣቶች ሚና የጎላ ነው ተባለ ከሁሉም ቤተ እምነት የተውጣጡ ወጣቶች ‹‹የክርስቲያንና ሙስሊም ግንኙነት ለሠላም- በወጣቶች›› በሚል መርህ የተዘጋጀ የሰላም ውይይት መድረክ ከድሬዳዋና ሐረር ከተማ ከተወጣጡ ወጣቶችና የሀይማኖት መሪዎች ጋር በድሬዳዋ ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኖርዌይ ቤተክርስቲያን የእርዳታ ድርጅት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት መድረክ ላይ ተሣታፊ የሆኑ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት ወጣቶች በተሰማሩበት መስክ ሁሉ ለሠላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ብለዋል፡፡ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ያለን ሀገር አንድ ነው፡፡ አንድ አይናማ በአፈር አይጫወትም ያሉት ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ የኢትዮጲያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሀፊ አንድ ሀገር ያለንና ሌላ ማምለጫ የሌለን…


