የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በተለያዪ የትምህርት መስክ በድህረና በቅድመ ምርቃት 2 ሺህ 93 ተማሪዎችን አስመረቀ።
የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በ2012 ዓ.ም በድህረና በቅድመ ምርቃት 728 ሴቶችና 1326 ወንድ በአጠቃላይ 2093 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርአቱ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደተናገሩት ባለፉት ጥቂት አመታት ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ በዩኒቨርስቲው አሳዛኝ የሆኑ ችግሮች ተፈጥረው የነበሩ ሲሆን በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈፀሙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ያቀፈ የማህበረሰብ አቀፍ አማካሪ ምክር ቤት…


