የመሬት ልማትና ማኔጀመንት ቢሮ በ2015 በጀት አመት ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል ትኩረት ሊሠጥበት እንደሚገባ ተገለጸ። ቢሮው የ2014 እቅድ የአፈጻጸም ሪፖርት እና የ2015 በጀት አመት እቅዱን በህዝብ ክንፍ አስገምግሟል።
በመድረኩም ከአስተዳደሩ የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፋ ሲሆን የአፈጻጸም ሪፖርትና እቅድ ቀርቦ ሠፊው ውይይት ተካሂዷል። ከመድረኩም ቢሮው እያከናወነ በሚገኘው የሪፎርም ስራ እያመጣ ያለው ለውጥ አበረታች መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን በቀጣይም የተቋቋመለትን አላማ ከዳር ለማድረስና የህብረተሰቡን ቅሬታው ከመቀነስ አኳያ ይበልጥ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ተመላክቷል። በተጨማሪም መረጃን ከኢንፎርሜሽን ኮምንኬሽን ቴክኖሎጂና ጋር ለማስተሳሰር እየተከናወነ የሚገኘው ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገልጿል።…


