በድሬዳዋ አስተዳደር በ2014 በጀት ዓመት የተጠናቀቁ ኘሮጀክቶች የምርቃት ስነ ስርዕት እየተካሄደ ነው።
በትላንትናው ዕለት መካሄድ የጀመረው በ2014 በጀት ዓመትበ1,2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውና በገጠርና በከተማ ተሰርተው የተጠናቀቁ 31 የልማት ፕሮጀክቶች የምርቃት ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለትም በገጠር ክላስተር ቀጥሏል። በምረቃ ስነ ስርዓቱ የተሳተፉ ሉዑካን ቡድን የአስተዳደሩ ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር የመሩ ሲሆን በአሰሊሶ ክላስተርና በለገኦዳ ጉዱንፈታ አነስተኛ መስኖ ፣በሁሉል ሞጆ የግድብና የካናል፣የሀሎ ቡሳና ለጎኦዳ ሚርጋ የመጠጥ ውሃ…


