ኢትዮጵያ በየዘመኑ ሲደርሱባት የነበሩትን ልዩ ልዩ ጫናዎች ተቋቁማ በከወነችው የዲፕሎማሲ ሥራ ከራሷ አልፋ ለአፍሪካውያንና ለሌሎችም ጥቁር ሕዝቦች ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክታለች፦ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ
የብልጽግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በፓርቲው ሁለተኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። የብልጽግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በመግለጫቸው ብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ከአንደኛው እስከ ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤው ያሉትን ስራዎች መገምገሙን ገልፀዋል፤ በዚህም የተላለፉ ውሳኔዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል። ሃላፊው በኢትዮጵያ በዲፕሎማሲና በውጭ ግንኙነት ዘርፍ የተገኙ ሀገራዊ…


