ሀገርን የሚወድ ሁሉ በበጎ ፍቃድ እና በአረንጓዴ አሻራ ስራ ላይ በመሳተፍ የዜግነት ድርሻቸውን መወጣት ይገባል ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ጥሪ አቀረቡ።
በድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ሰራተኞች እና የዘርፉ ባለሞያዎች የአረንጎዴ አሻራ መርሃ ግብር በማሪያም ትምህርት ቤት አከናውነዋል። በዘንድሮው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር 7 መቶ ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቀዶ እየተሰራ ነው። በድሬዳዋ አስተዳደር የዚሁ አንድ አካል የሆነው የክረምት አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ሰራተኞች እና የዘርፉ ባለሞያዎች እና ባለድርሻ አካላቶችን ባሳተፈ…


