ህገ ወጥና መርህ አልባ ግብይትን በመቆጣጠር የዋጋ ንረትን ማረጋጋት እንደሚገባ የድሬዳዋ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ገለጹ።
በንግድ ዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ለመከታተልእና ድጋፍ ለማድረግ የሚበጅ የቁጥጥር ስርዓት በቢሮው መዘጋጀቱ ተገልጿል። በአገራችን ባለፉት አመታት ፈጣን ልማትና መልካም አሰተዳደር ስርአት ለመገንባት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲሁም ፕሮግራሞች በመቅረፅ የማሻሻያ ስራዎች መሰራታቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ፥የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ሀርቢ ቡህ ገልፀዋል። የንግድ አሰራር ስርአቱ አሁን ያለበት ሁኔታ ሲታይ አንዳንድ በንግድ ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና…


