የምግብ ዋስትና ችግር ዓለምን ወደ ከፋ ቀውስ የሚመራ ትልቅ ፈተና ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ
አካባቢን በማልማት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ አለመቻል ተስፋ መቁረጥን በመፍጠር ወደ ግጭት፣ ሽብርተኝነት እና ፍልሰት የሚያመራ የዓለም ስጋት መሆኑን የጣሊያን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሚኒስትሮች ምክርቤት ፕሬዚዳንት ጆርጂያ ሜሎኒ ገለጹ። በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ሁለተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ ላይ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሯ፥ ጉባኤው በአፍሪካ ሲካሄድ የመጀመሪያው መሆኑን ጠቅሰው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ…


