2025
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የአስተዳደሩ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሰብዓዊ ተልዕኮ እንዲሳካ ላበረከቱት የላቀ አበርክቶ ዕውቅና ተሰጣቸው።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሐር አስተዳደሩ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሰብዓዊ ተልዕኮ እንዲሳካ ላበረከቱት የላቀ አበርክቶ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላ ለድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከማህበሩ የበላይ ጠባቂ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የተበረከተና አስተዳደሩ ለድሬዳዋ የቀይ መስቀል ላደረገው ድጋፍ የተዘጋጀውን እውቅና ማረጋገጫ አስረክበዋል ። የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሀር ማህበሩ ለሰጣቸው…
በሰላም ግንባታና ግጭት አፈታት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በጅጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል
ሴንተር ፎር ሪስፖንሲብል ኤንድ ፒስፉን ፖለቲክስ ከሂራድ ፐብሊክ ፖሊሲ ጥናት ተቋም ጋር በመቀናጀት ያዘጋጁት “የመገናኛ ብዙሀን እና የጋዜጠኞቾ ሚና በግጭት መከላከል እና ሰላም ግንባታ በዲጂታል ዘመን” በሚል መሪ ሀሳብ የምክክር መድረክ በሱማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በዚህም በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀሙድ በተለያዩ አለመግባባቶች የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለማረጋጋት ሚዲያ ያለው…
2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል፡፡ በጉባዔው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪ የጣሊያን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ እንዲሁም የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ተገኝተዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሃመድ፣ የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ፣ የዓለም…
ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የምግብ ሥርዓት በመከተል ፍላጎታችንን ለማሳካት እየሰራን ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የምግብ ሥርዓት በመከተል የወደፊት ፍላጎታችንን ለማሳካት እየሰራን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ስትራቴጂና ፖሊሲዎችን ቀርፃ ተግባራዊ እያደረገች ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው የተመድ የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በኋላ፣ ከሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር…
ዓለም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በአንድነት የሚቆምበት ጊዜው አሁን ነው፦ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ
ዓለም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በአንድነት የሚቆምበት ጊዜው አሁን ነው ሲሉ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ገለፁ። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በመካሄድ ላይ ባለው 2ኛው የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ላይ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የምግብ ሥርዓታችን አሁን ከመቼውም በላይ በፈተና ውስጥ ያለ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ አካታች የሆነ የምግብ ሥርዓት ለማረጋገጥ በትብብር መስራት አስፈላጊ…
ኢትዮጵያ በመደመር ያሳካችውን ለጉባኤው ለማጋራት ዝግጁ ነች፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ስታስተናግድ እንደ መሰብሰቢያ ብቻ ሳይሆን ሁሉን አካታች በሆነው መደመር ያሳካቻቸውን ግቦች እና ዓላማዋን ለማጋራት ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ተሳታፊዎች በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት የእራት ግብዣ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእራት ግብዣው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ “የተሰባሰብነው ራት…
የናፍቆት ድሬ መርሀ ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችን የሚያቆራኝ እና አብሮነትን የሚያሳይ መሆኑን የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ተናገሩ።
የናፍቆት ድሬ ሳምንት በዘንድሮው ዓመት ለአራተኛ ጊዜ መከበር ጀምሯል ። በመጀመሪያ ቀን መርሀግብር “የናፍቆት በድሬ ፌስቲቫል” በነምበርዋን ኮሪደር ልማት ላይ በአስተዳደሩ የሚኖሩ የብሄር ብሄረሰቦች የባህል እና የወግ እቃዎች ትዕይንት እና የጣፋጭ ምግቦች ቅምሻ ተካሂዷል። ፌስቲቫሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተገኝተው አስጀምረውታል። ለተሳታፊዎች ስለመርሀግብሩ ገለፃ እየሰጡ እና ከጣፋጭ ምግቦቹ እያስቀመሱ ባማረ ሁኔታ ተካሂዷል።…
ሀገራት ለብዝኀ ሕይወት እና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት በመስጠት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ አለባቸው፡- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ በበይነ መረብ ለታዳሚዎች ባስተላለፉት መልዕለክት፤ ሀገራት ለብዝኀ ሕይወት እና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት በመስጠት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ አለባቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ እና ጣሊያን ከተመድ ጋር በመተባበር 2ኛውን የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በጋራ በማዘጋጀታቸው ዋና ጸሐፊው አመስግነዋል፡፡ ሀገራት በመደበኛ በጀታቸው ውስጥ ለአካባቢ ጥበቃ እና የብዝኀ ሕይወት…


