March 2026
አፋር የተፈጥሮ ድንቃድንቅ የታደለች የምድራዊ ገነት መገኛ ናት፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*********************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፋር ክልል የሚገኘውን ልዩ የተፈጥሮ ጸጋና የለመለመ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ምርቃት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ክልሉ በታሪክና በተፈጥሮ የታደለ መሆኑን ገልጸዋል። ጥቅጥቅ ብሎ የበቀለውና ለየት ያለ ቅርጽ ያለው የፓልም ጫካ፣ በአካባቢው የሚፈሰው የተፈጥሮ ፍልውኃ፣ ውብ ተራራዎችና ልዩ የሳር ዝርያዎች ለሺህ ዓመታት የቆዩ ድንቅ ሀብቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል። እነዚህን የተፈጥሮ ምስጢሮች…
በድሬዳዋ አስተዳደር በስፋት እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ዝርዝር መረጃ
ድሬን ፅዱ፣ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የኮሪደር ልማት ስራዎች በጥራትና በፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በከተማችን እስካሁን በኮሪደር ልማት ስራ የተጠናቀቁ የመንገድ እና ሌሎች መሰረተ ልማት ስራዎችን ስንመለከት:- • 21 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ግንባታ • 18 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገድ ግንባታ • 22 ኪ.ሜ የመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማት ስራ • 6.20 ኪ.ሜ የመንገድ አካፋይ ማስፋት እና ግንባታ…
የነዳጅ ብክነት እንዳይኖር ሁሉም ዜጋ ተገቢ ያልሆኑ የነዳጅ አጠቃቀሞችን በማሶገድ ነዳጅን በኃላፊነትና በቁጠባ ሊጠቀም ይገባል።
መጋቢት 10/2018 ዓ.ም ለመሆኑ ተገቢ ያልሆኑ የነዳጅ አጠቃቀሞች የትኞቹ ናቸዉ? 1ኛ:- መኪናው ሳይንቀሳቀስ ሞተሩን ብቻ አስነስቶ መቆየት። መኪናው ሳይንቀሳቀስ ሞተር አስነስቶ ለረጅም ደቂቃዎች መቆም በዜሮ ኪሎ ሜትር እየተጓዙ ነዳጅ ማቃጠል ነው። 2ኛ:- ከመጠን በላይ የሆነ ፍጥነት:: መኪና በከፍተኛ ፍጥነት ሲነዳ የንፋስ ግፊት ስለሚጨምር ሞተሩ ያንን ተቋቁሞ ለመጓዝ ብዙ ነዳጅ ይጠቀማል። 3ኛ:- በድንገት ፍጥነት መጨመርና በድንገት…
‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ሁሉን አቀፍ ምድራዊ ገነት!
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ’ገበታ ለትውልድ’ ውጥን አካል የሆነው ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’፤ ማህበረሰብን ለማበልጸግና ሀገራዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የባለራዕይ መሪ የአመራር ጥበብና ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ምስክር ነው። ሎጅው በተለያዩ የፍራፍሬ እና የደን ዛፎች በለመለመ 78,000 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፤ ተፈጥሯዊ የ”ሰማያዊ ዓይን” ፍልውሃ መዋኛ ፣ ሁለት ግዙፍ ሰው ሰራሽ…
“የመራጭነት ካርዳችንን በመውሰድ የነገዋን ኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ዛሬ መወሰን አለብን” አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
7ተኛውን አገራዊ ምርጫን በማስመልከት በብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ለምርጫ በሚወዳደሩበት ወረዳ በቢዮ አዋሌ ክላስተር የምርጫ ካርዳቸውን በመመዝገብ ወስደዋል። በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ ለመራጭነት መመዝገብ በሀገርዎ ጉዳይ ላይ የመወሰን ሥልጣን እንዳለን የምናረጋግጥበት መብት ነው ብለዋል። ዜጎች አገር ወዳድነታቸውን በተግባር ከሚያሳዩባቸው መንገዶች በምርጫ ንቁ ተሳታፊ መሆን አንዱ ሲሆን፤ ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ ለሀገረ መንግሥት…
የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል
በምርጫው የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የድሬዳዋ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት አስታወቀ። ፓርቲዎች የፖሊሲ ሀሳቦቻቸውን ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊና ሰላማዊ እንዲሆን የድርሻውን እየተወጣ መሆኑንም ገልጿል። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጣሂር ሮብሌ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ዘንድሮ በሚካሄደው 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለተካ ፓርቲዎች የድርጅቱን የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ተጠቅመው አማራጭ…
የቻይና ኢንቨስተሮች በድሬደዋ የተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ተገለፀ::
በኢትዮጵያ የቻይና ኢምባሲ ምክትል አምባሳደር ሚስተር ሱን የተመራ ልዑክ በድሬደዋ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ጉብኝት ያደረገ ሲሆን ከአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል። በውይይቱ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፉ አቶ ገበየው ጥላሁን ድሬዳዋ ከአራት የቻይና ከተሞች ጋር የህትማማች ግንኙነት እንዳላት ገልፀው በአስተዳደሩ የቻይና ባለሀብቶች በፌደራል መንግስቱ በኩል በበርካታ የኢንቨስትመንትና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ፍላጎት እንደለ…
የመደመር አንቀፅ
እንቅስቃሴ የከተሞች ሕይወት ነው። አንድ ከተማ የከተማነት ሕይወት እንዲኖራት በከተማዋ ውስጥ የንግድ፣ የባህል፣ የስፖርት፣ የአስተዳደር፣ የዲፕሎማሲ፣ የእምነት፣ የኮንፈረንስ፣ ወዘተ እንቅስቃሴዎች መኖር አለባቸው። እነዚህ እንቅስቃሴዎች የከተማዋን ገቢ ይጨምሩታል። ለከተማዋ ነዋሪዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ። ከተማዋን የብዙዎች መናኸሪያ እና የኅብረ ብሔራዊ አንድነት መፍጠሪያ ያደርጓታል። የከተማዋን በጎ ገጽታም ያስተዋውቃሉ። እነዚህን እንቅስቃሴዎች ለማሣለጥ የተለያዩ የመጓጓዣ አማራጮችን በከተሞቻችን መገንባት ያስፈልጋል። ከጤናና…


