2026
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሳይንስ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ዘመናዊ የምርምር ማዕከል ዛሬ መርቀን ከፍተናል። በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው ይህ ዘመናዊ ተቋም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፤ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው። የምርምር ማዕከሉ 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) ቦታዎችን፣ እንዲሁም…
አርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ውስጥ የተገነባው አዲሱ ዘመናዊ የምርምር ሕንፃ እና ፋይዳዎቹ:-
– 34 ዘመናዊ ላቦራቶሪዎች – የላቁ የጄኖሚክስ (genomics) እና የባዮኢንፎርማቲክስ (bioinformatics) መሠረተ ልማቶች፣ – የባዮኢኩዊቫለንስ (bioequivalence) ማዕከልን አካቷል። ተቋሙ ለሥልጠና እና ለምርምር የተመደቡ ቦታዎችን የያዘ ሲሆን በኢትዮጵያ እና በመላው አፍሪካ ለሳይንስ ሥነ ምሕዳር መስፋፋትና አቅም ግንባታ አዲስ መለኪያ አስቀምጧል።
“ኢትዮጵያ ክትባት ማምረት አትችልም” የሚለውን ምልከታ የቀየረው የምርምር ማዕከል
ኢትዮጵያ በመድኃኒትና በክትባት ምርት ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ግዙፍ የምርምር ማዕከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ተመርቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማዕከሉን በመረቁበት ወቅት፥ ከዚህ ቀደም ይህን መሰል መሰረተ ልማት ባለመኖሩ “ኢትዮጵያ መድኃኒትና ክትባት ማምረት አትችልም” በሚል የምናቀርበውን የአጋርነት ጥያቄ ብዙዎች ሳይቀበሉት ቀርተዋል ብለዋል። የዚህ ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መገንባት ያንን…
“በአምስት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን መድኃኒት ሙሉ በሙሉ በራሷ አቅም ታመርታለች” – ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)::
በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን መድኃኒት ሙሉ በሙሉ በራሷ አቅም እንደምታመርት ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባውን ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መርቀው በከፈቱበት ወቅት ኢትዮጵያ በመድኃኒት ምርት ራስን ለመቻል የሄደችበትን ርቀት አብራርተዋል። በአንድ ሀገር ውስጥ ችግር እና ተግዳሮቶች ሲፈጠሩ ከመሸበር ይልቅ ችግሩን እንደ ዕድል መጠቀም እንደሚያስፈልግ…
የ8 አመታት ስኬታማ የዲፕሎማሲ ጉዞ እና የመጋቢት 24 ፍሬዎች ምን ይመስላል? ድሬዳዋስ በዘርፉ ምን አሳካች?
መጋቢት 24 የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ በሀገር ውስጥ ልማት ብቻ ሳይወሰን፣ በዲፕሎማሲው መስክም አስደማሚ ድሎችን አምጥቷል። የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) “መደመር” እሳቤ ሀገራችንን ከገለልተኝነት ወደ ንቁ ተሳትፎና መሪነት አሸጋግሯታል። ባለፉት ስምንት ዓመታት ያገኘናቸው ዲፕሎማሲያዊ እውቅናዎችና አጋርነቶች የአመራሩ ብስለትና የጸና ሀገራዊ ፍቅር ውጤቶች ናቸው። በለውጡ ዓመታት ኢትዮጵያ የነበረባትን የዲፕሎማሲ ከበባ በመስበርና ብሔራዊ ጥቅሟን በማስከበሩ ረገድ…
ኢትዮጵያ ዐዲሲቷ የተስፋ ዓድማስ ናት!
መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በ21ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ የታሪክ አውድ ውስጥ አዲስ ትርጉምና ጽኑ ቃል-ኪዳን ተላብሶ ብቅ ያለ፣ ለሀገራችንና ለሕዝቦቿም አዲስ የተስፋ አድማስን የፈነጠቀ ክስተት ነበር። ይህ ዕለት ኢትዮጵያን ተብትቦ ይዞ ከነበረው ውስብስብ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቅርቃር አውጥቶ ወደ ብሩህ መጻኢ ዕድል ለማሸጋገር የተገባ ታላቅ የትውልድ…
ከመጋቢት እስከ መጋቢት የማትበገረው ኢትዮጵያ
********************** “ስለ አለፈ ዘመናችን ስንናገር ከሚሰማን ኩራት ጋር ሲነጻጸር፣ ነገ የሚጠብቀን ተስፋ ቢበልጥ እንጂ አያንስም። ዋናው ጥያቄ ተስፋውን አይተን እውን ለማድረግ ምን ያህል ቁርጠኞች ነን? የሚለው ነው። ኢትዮጵያ የምትበለጽገው እኛ ለመለወጥ በፈለግንበት መጠንና የጋራ ራዕይ በሰነቅንበት ልክ ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ካዘመመችበት ቀና የምትልበት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ይኼን ለማሳካት የዛሬ ህያው ኢትዮጵያውያን ታላቅ አደራ ተጥሎብናል።” ጠቅላይ…
ኢትዮጵያ በፈተና ውስጥ የጸናች አይበገሬ ሀገር
*********************** መጋቢት ለኢትዮጵያውያን የድል መባቻና የለውጥ ወጋገን የቀደደበት ወር ነው። ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት ሀገራችን ሕልውናዋን የሚፈታተኑ “የሦስትዮሽ መከራዎችን” (Triple Shocks) ማለትም ደም አፋሳሽ ጦርነትን፣ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጫናን እና የተፈጥሮ ፈተናዎችን በጽናት ተሻግራለች። ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብለው ያሟረቱ ሁሉ የሕዝቧን አይበገሬነት ዘንግተውት ነበር። ዛሬ ግን ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር አዳዲስ ታሪኮችን እየጻፍን እንገኛለን፦ ከስንዴ ተረጂነት…
<<ድሬዳዋን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ቱሪስቶች ሳቢ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ነው።>>
አቶ ሀርቢ ቡህ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ #DGC | መጋቢት 23 /2018 በድሬዳዋ አስተዳደር በሆቴልና ቱሪዝም እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ በግንባታ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ የመስክ ምልከታ አካሂደዋል። ድሬዳዋን የቱሪስት እና የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በሆቴል ኢንቨስትመንት ዘርፍ በርካታ…


