የድሬዳዋን የአብሮነትና መደጋገፍ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ::
የሆር ሙድ ጤና ቡድን 1447ኛው የረመዳን ፆም አስመልክቶ የተለያዩ የፍጆታ እቃዎች ድጋፍ አበርክቷል።በመረሀ ግብሩ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተጋባዥነት ተገኝተዋል። በድጋፉ መረሀ ግብሩ ተጋብዘው የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር እንደተናገሩት በአገር አቀፍ ደረጃ የማእድ ማጋራት የበጎ ፍቃድ ስራዎች በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተነሳሽነት መከናወን ከጀመረ ወዲህ በርካታ ተግባራት እየተፈፀሙ እንደሆነ ጠቁመዋል።…


