ኢትዮጵያ ስማርት የፖሊስ አገልግሎትን በማስጀመር በአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ናት – ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል
ኢትዮጵያ የሰው አልባ (ስማርት) ፖሊስ አገልግሎትን በማስጀመር በአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር መሆኗን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለፁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል። ኮሚሽነር ጀነራሉ ይህን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ይህ አገልግሎት የሕግ ማስከበር ስራን ወደ ዲጂታል በማሸጋገር ህብረተሰቡ ያለምንም እንግልትና…


