የ2019 ረቂቅ በጀት ከ2.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ሆኖ እንዲቀርብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 56ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ምክር ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል። የ2019 የፌዴራል መንግሥት በጀት የዐሥር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነው የ2019-2021 የልማት እና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፊሲካል ማዕቀፍን…


