አፋር የተፈጥሮ ድንቃድንቅ የታደለች የምድራዊ ገነት መገኛ ናት፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*********************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፋር ክልል የሚገኘውን ልዩ የተፈጥሮ ጸጋና የለመለመ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ ምርቃት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ክልሉ በታሪክና በተፈጥሮ የታደለ መሆኑን ገልጸዋል። ጥቅጥቅ ብሎ የበቀለውና ለየት ያለ ቅርጽ ያለው የፓልም ጫካ፣ በአካባቢው የሚፈሰው የተፈጥሮ ፍልውኃ፣ ውብ ተራራዎችና ልዩ የሳር ዝርያዎች ለሺህ ዓመታት የቆዩ ድንቅ ሀብቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል። እነዚህን የተፈጥሮ ምስጢሮች…


