የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ሽግግር እና ኒዩትሪሽን ንቅናቄ በድሬዳዋ አስተዳደር በይፋ መተግበር መጀመሩ ተበሰረ::

​የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ATI) ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር በመተባበር ለመጪዎቹ አምስት ዓመታት የሚተገበር “የምግብ ሥርዓት ሽግግር ፍኖተ-ካርታ” ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አከናወነ። ይህ ፍኖተ-ካርታ በአስተዳደሩ በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖረውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግና የተመጣጠነ የምግብ ስርዓት እንዲኖር የሚያግዝ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል። ​የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዶ/ር ሰይፉ ታደሰ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት የፍኖተ-ካርታው ራዕይ በከተማም ሆነ…

Read More

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገብቷል።

ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር እና ክብርት አዳነች አቤቤን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የተካተቱበት ልዑክ ጅግጅጋ ከተማ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላለፈ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል። 1ኛ:- ካቢኔው በቀዳሚነት የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ፕላን ሥራዎች ላይ በመወያየት ውሳኔ አስተላልፏል። የከተማ ፕላን ሥራዎች የድሬዳዋን ፈጣን ዕድገት በስልታዊ መንገድ ለመምራት ከፍተኛ ሚና አላቸው። የመኖሪያና የንግድ ቀጠናዎችን በዘመናዊ አሠራር በመለየት ለቀጣይ መሠረተ ልማት፣ ለኢንቨስትመንት መስፋፋት እና ለከተማዋ ውበት ምቹና ዘላቂ መሠረት…

Read More

​የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጅሃር በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በዛሬው ዕለት በግንባር ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል።

ከንቲባው ድምፃቸውን የሰጡት በአስተዳደሩ ወረዳ 04 በሚገኘው ምርጫ ጣቢያ አንድ ነው። ​ከንቲባ ከድር ጁሃር ድምፅ በሰጡበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዜጎች በሕገ-መንግስቱ የተሰጣቸውን የመምረጥ መብት በአግባቡና በሃላፊነት ስሜት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስበዋል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በአገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን የገለጹት ከንቲባው፤ መላው ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥና የአገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ…

Read More

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ ድሬዳዋ ገብተዋል::

ክቡር አቶ አደም ፋራህ ድሬዳዋ የገቡት በሶማሌ ክልል በሽንሌ ከተማ ድምፅ ለመስጠት ነው። የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ፣የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ይሱፍ እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Read More