ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ትምህርት እየተሰጠ ነው

ነገ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት ይረዳ ዘንድ ስልጠና ወስደው የተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች በመላው ሀገራችን የመራጮች ትምህርት እየሰጡ ይገኛሉ። በድሬዳዋ ከተማም በገጠር ክላስተሮችና በከተማዋ ውስጥ በጎ ፈቃደኞች በመንቀሳቀስ ይህንን ትምህርት እየሰጡ መሆናቸው ታውቋል። አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎችም እየተሰጠ ያለው ትምህርት በቂ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ገልጸው፣ ይህም በምርጫው ዕለት ያለምንም ስህተት አስፈላጊውን ድምፅ ለመስጠት እንደሚረዳቸው አስታውቀዋል።

Read More

የድሬዳዋ የሌሊት ታክሲ ማህበር ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ሊሰጥ ነው

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የፊታችን ሰኞ የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ የድሬዳዋ የሌሊት ታክሲ ማህበር አስታወቀ። መራጩ ማህበረሰብ ያለምንም እንግልትና የትራንስፖርት ችግር ሳይገጥመው ድምጹን መስጠት እንዲችል ማህበሩ ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አሽከርካሪዎች ገልጸዋል። የማህበሩ አስተባባሪ ወጣት ቃልኪዳን ፀሐይ እንደገለፀው፣ ማህበሩ በአጠቃላይ 500 አባላት ያሉት ሲሆን ሁሉም አባላት የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውንና…

Read More

በድሬዳዋ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማሰራጨት ሥራ ተጀመረ::

በድሬዳዋ አስተዳደር ለሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የሚያገለግሉ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማሰራጨት ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ​የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዚያድ ያሲን መሀመድ ለድሬዳዋ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንደገለጹት፤ ለምርጫው የሚያገለግሉ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች፣ ሳጥኖች እና መከለያዎች በአራቱም የገጠር ክላስተሮች በሚገኙ 130 የምርጫ ጣቢያዎች እየተከፋፈሉ ይገኛሉ።…

Read More

የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገለጹ

የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ የዜግነት መብታቸውን ለመጠቀምና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማጠናከር በሂደቱ ላይ በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል። የወሰዱትን የመምረጫ ካርድ በጥንቃቄ በመያዝ ቀኑን እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ያመላከቱት ነዋሪዎቹ፤ የምርጫው ሂደት ሥነ-ሥርዓትና በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አብራርተዋል። በከተማዋ የሚገኙ ለመጀመሪያ ጊዜ…

Read More

የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ሰኞ የሚካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ገለጹ::

የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24 የሚካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል። አስተያየታቸውን ለኢቢሲ የሰጡ ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ መራጩ ሕዝብ ለሀገር ሰላም፣ አንድነትና ዕድገት ያግዛል ያለውን ለመምረጥ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል። ከተሳታፊዎቹ መካከል ወጣት ዳግማዊት አዲሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የመምረጥ ዕድል በማግኘቷ ቀኑን በጉጉት እየጠበቀችው መሆኗን ገልጻ፣ ለመምረጥ መዘጋጀቷን ተናግራለች። በተመሳሳይ መልኩ፣ ሙፈርያት ታዬ ለመምረጥ…

Read More

የድሬዳዋ ፖሊስ ከለውጡ ማግስት ዘርፈ-ብዙ የሪፎርም ስራዎችን ማከናወኑ ተገለጸ::

​የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ አመራሮችና አባላት የማዕረግ ማልበስ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት አካሂዷል። ​በዚሁ የማዕረግ ማልበስ መርሃ-ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር፤ በዛሬው ዕለት የማዕረግ ዕድገት ያገኙ የፖሊስ ኮሚሽኑ አመራሮችና አባላት ከዚህ ቀደም ከነበራቸው ተነሳሽነት በበለጠ በመሥራት፣ ነዋሪውን ማኅበረሰብ በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል እንደሚገባቸው አሳስበዋል። ​ክቡር ከንቲባው አክለውም፣…

Read More

ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የድሬዳዋ-ሺኒሌ አስፓልት መንገድ በይፋ ተመረቀ

በድሬዳዋ አስተዳደር እና በሶማሊ ክልል መካከል ያለውን የንግድና የማህበራዊ ትስስር ይበልጥ ያጠናክራል ተብሎ የሚጠበቀው የድሬዳዋ-ሺኒሌ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ተጠናቆ በይፋ ተመረቀ። ለዚህ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ታውቋል። የመንገድ ፕሮጀክቱን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደን ፋራህ እንዲሁም የሶማሊ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት በላቀ ውጤት መቀጠሉን ገለጹ

የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት በላቀ ውጤት መቀጠሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱልልታ ወረዳ በመገኘት፣ በ2 ሺህ 150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ማሳን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጉብኝታቸው ወቅትም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የሀገርን የምግብ ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

Read More

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ድሬዳዋ ገቡ

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ በዛሬው እለት ድሬዳዋ ገብተዋል ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀሙድ ፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ…

Read More

ብልፅግና ፓርቲ ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር በማረጋገጥ ውጤት ተኮርነቱን በተጨባጭ ያስመሰከረ መሆኑ ተገለፀ::

“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል፣ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የሻይ ቡና መርሃ ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 03 ተካሂዷል። በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ወርቅነህ፤ ብልፅግና ፓርቲ ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር በመፈፀም፣ ለቃሉ የታመነ እና በስራው ውጤት ተኮርነቱን በተጨባጭ ያስመሰከረ ፓርቲ መሆኑን ገልፀዋል።…

Read More