Amharic
በነገው ዕለት በሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን የድሬዳዋ ነዋሪዎች ገለጹ::
በነገው ዕለት በመላ ሀገሪቱ የሚከናወነውን ሰባተኛ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ያነጋገራቸው የወረዳ አንድ ነዋሪዎች ገለጹ። የምርጫ ካርድ የበይነ-መረብ (ኦንላይን) መተግበሪያ ተጠቅመው መውሰዳቸውን የሚናገሩት የወረዳ 01 ነዋሪው አቶ ረመዳን ሰይድ፤ ለነገው ዕለት ከየትኛውም ጉዳይ በላይ ቅድሚያ በመስጠት፣ በአምስት ዓመት አንድ ጊዜ የሚገኘውን የመምረጥ ዕድል በጠዋት ለመጠቀም መወሰናቸውን…
ነገ ለሚደረገው 7ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የሚበጀንን ለመምረጠ ተዘጋጀተናል ሲሉ የወረዳ 2ነዋሪዎች ገለፁ::
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንዱን እና ትልቁን ዲሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅቷን አጠናቃ ዜጎች ይበጀኛል ያሉትን ድምፅ ለመስጠት ሰዓታት ብቻ ቀርተውታል። 7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ነገ ግንቦት 24/2018 ዓ/ም ይካሄዳል ምርጫውን ለማካሄድም በአስተዳደሩ በወረዳ 02 የሚገኙ ነዋሪዎች የሀገሪቱ ሰላምና ልማት ያስቀጥላል የምንለውን ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ስሉ ገልፀዋል። ህብረተሰብም ነገ ለሚደረገው ምርጫ በነቂስ ወጥቶ በካርድ የሚበጀውን ድምፅ በመሰጠት…
7ኛው ጠቅላላ ምርጫን ለመምረጥ በጉጉት እየተጠባበቁ መሆኑን የወረዳ 5 እና የወረዳ 6 ነዋሪዎች ገለፁ
በህዝብና በሀገር ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ሁነቶች መካከል ምርጫ አንዱ ነው። ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደውን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከቅድመ ምርጫው ጀምሮ እስከ ምርጫው እለት ድረስ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር የወረዳ 5 እና የወረዳ 6 ነዋሪዎች ገለፁ። የምርጫ ካርዴን በወቅቱ ወስጃለሁ፤ የዘንድሮን ምርጫ ለመምረጥ ሙሉ በሙሉ…
ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ አግባብ እንዲካሄድ የበኩላቸውን አስተዋፆ እንደሚወጡ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች አስታወቁ
የወረዳ 04 አስተዳደር ነዋሪዎችም በነገው እለት በሚካሄደው 7 ተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫም ለሀገራችን እንዲሁም ደግሞ ለአስተዳደራችን በቀጣይ አመታት የተሻለ ስራዎችን ይሰራል ብለን ያመኑበትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። 7 ተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫም ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ አግባብ እንዲካሄድ የበኩላቸውን አስተዋፆ እንደሚወጡ ነው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ያስታወቁት ።በነገው እለትም ከማለዳው 12 ሰዓት አንስቶ ነዋሪው ህብረተሰብ…
በድሬደዋ አስተዳደር ወረዳ 8 የምርጫ ዝግጅት ምን ይመስላል….!!
ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀጣዩን የእድገት፣ የሰላምና የዲሞክራሲ ምዕራፍ የምታረጋግጥበት ታሪካዊው ሀገራዊ ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ እየተቃረበ ይገኛል። ምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ደግሞ የቅድመ ምርጫ ዝግጅቶች ወሳኝ ሚና አላቸው። በአሁኑ ወቅት በድሬደዋ አስተዳደር የምርጫ አስፈጻሚ አካላት፣ የጸጥታ መዋቅሩ እንዲሁም መላው ማህበረሰብ ለዚህ ትልቅ ሀገራዊ ኩነት በአንድነት እየተዘጋጁ ይገኛሉ። በአስተዳደሩ ወረዳ 8 ነዋሪ ወጣት አብዱልጀባር አህመድ…
የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች ነገ ማለዳ 12:00 ሰዓትን በከፍተኛ ጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸውን ገለፁ
ሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ ዛሬ በዋዜማው የመላው ድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች በዲሞክራሲ፣ በሰላም እና በነፃነት ለመምረጥ ሙሉ በሙሉ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል። ህዝቡ የዜግነት ኃላፊነቱን ለመወጣት እና የወደፊት እጣ ፈንታቸውን ለመወሰን ነገ ጠዋት 12:00 ሰዓት ላይ የምርጫ ጣቢያዎች የሚከፈቱበትን ታሪካዊ ቅጽበት በከፍተኛ መነቃቃት እየተጠባበቁ እንደሚገኙም ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል። አስተያየታቸውን የሰጡ እናቶች፣…
‘በምርጫ ካርዳችን መብታችንን ለመጠቀም ተዘጋጅተናል”የወረዳ 07 እና 09 ነዋሪዎች
ወ/ሮ አረጋሽ ተካ በድሬዳዋ አስተዳደር የ07 ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በቡና ንግድ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።ምርጫ የነገውን እጣፈንታችንን የምንወስንበት ዲሞክራሲያዊ መብታችንን የምንተገብርበት እንደሆነ አምናለው ይላሉ። በመሆኑም ነገ በሚደረገው ምርጫ ቀድመው በወሰዱት የምርጫ ካርድ የሚበጀኝን ለመምረጥ ተዘጋጅቻለው ሲሉ ገልጸዋል። እንደ እሳቸው ሁሉ የ09 ቀበሌ ነዋሪው አቶ አብዱልፈታህ ሼህ አብዱረህማን ቀደም ሲል ሁለት አጠቃላይ አገራዊ ምርጫ መሳተፋቸውን ገልፀው የዘንድሮው…
በድሬዳዋ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ይገኛል። በነገው ዕለት ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለድምፅ አሰጣጡ የተሟላ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል። በዚሁ መሰረትም በአስተዳደሩ የምርጫ ቁሳቁስ ከትናንት ጀምሮ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዚያድ ያሲን…


