የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ወርቅነህ ለ85ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች የድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ያስተላለፉት መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል:- ============ መላው የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎችና የሀገራችን ሕዝቦች፤ እንኳን ለ85ኛው የአርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! እንኳን አደረሰን! የአርበኞች የድል በዓል፤ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ፋና የሆኑት አባቶቻችንና እናቶቻችን፣ የግፍ ወረራን በፅናትና ባልተገደበ መስዋዕትነት ድል ያደረጉበት የታሪክ አሻራ ነው። አርበኞቻችን ያኔ በዱር በገደሉ የተዋደቁት ለሰንደቅ ዓላማ ክብር ብቻ ሳይሆን፣ እኛ ዛሬ አንገታችንን ቀና…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ለ85ኛው የአርበኞች ድል መታሰቢያ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ያስተላለፉት መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል መላው የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎችና የሀገራችን ሕዝቦች፤ እንኳን ለ85ኛው የአርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን! ይህ ታላቅ የድል በዓል አባቶቻችንና እናቶቻችን፣ እንዲሁም በየዘመናቱ የነበሩ ወጣቶቻችንና እህቶቻችን ለታላቋ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት የከፈሉትን ወደር የሌለው መስዋዕትነት የምንዘክርበት ታሪካዊ ዕለት ነው። አርበኞቻችን ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን ትተው በጋራ በመቆማቸው ሀገርን ከወራሪ ማዳን…

Read More

እንኳን ለ85ኛው የዐርበኞች ድል በዓል አደረሳችሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ85ኛው የዐርበኞች ድል በዓል የአደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦ እንኳን ለ85ኛው የጀግኖች ዐርበኞች በዓል አደረሳችሁ ሚያዝያ 27 ቀን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ዐርበኞች የፋሽስትን ወረራ የቀለበሱበት እና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ያስከበሩበት በዓል ነው። ዐርበኝነት ማለት ለሀገር ያለ ዋጋ የሚከፈል ከራስ ወዳድነት የነጻ መሥዋዕትነት ነው።…

Read More

በመሠረተ ልማት ዝርጋታ የገጠሩን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል!!

ባለፉት ስምንት ዓመታት መንግሥት በመንገድ፣ በመስኖና በውሃ ዘርፎች ላይ ባደረገው ከፍተኛ የበጀት ድልድል የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ ለማሻሻል ሰፊ ሥራዎችን አከናውኗል። በመንገድ ዘርፍ በ2010 ዓ.ም የነበረው የ126,773 ኪ.ሜ ሽፋን በስምንት ዓመታት ውስጥ ወደ 180ሺህ 232 ኪ.ሜ በላይ አድጓል።ይህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ53ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አዳዲስ መንገዶች ተገንብቶ ለሀገሪቱ ልማት ዉሏል ማለት ነው፡፡ ከለውጡ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ልዑክ በሐረሪ ክልል ያደረገው የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርና የፖለቲካ ንቅናቄ መድረክ በስኬት ተጠናቀቀ::

በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጅሃር የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በሐረሪ ክልል ያደረገውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከሪያ ጉብኝት በስኬት አጠናቋል። ጉብኝቱ በሁለቱ አጎራባች አካባቢዎች መካከል ያለውን ታሪካዊና ማኅበራዊ ትስስር ከማጠናከር ባለፈ፣ በጋራ የልማትና የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጅሃር በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፤ “ድሬዳዋና ሐረሪ በጂኦግራፊ ብቻ ሳይሆን በታሪክ፣…

Read More

ከንቲባ ከድር ጁሀር በድሬዳዋና ሐረሪ አመራሮች የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ግብ አስቆጠሩ

በድሬዳዋ አስተዳደር እና በሐረሪ ክልል አመራሮች መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ በሐረር ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ ታላቅ ስፖርታዊ መድረክ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ባሳዩት ልዩ ብቃት ግሩም ግብ ማስቆጠር ችለዋል። የከንቲባው ግብ የመሪዎችን ንቁ ተሳትፎና የአካል ብቃት ጥንካሬ ከማሳየቱም በላይ፣ በሁለቱ ወንድማማች አመራሮች መካከል…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደርና የሐረሪ ክልል አመራሮችን ያሳተፈና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ደማቅ ስፖርታዊ ውድድር በሐረር ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል

በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የተመራ ልዑካን ቡድን ሐረር ከተማ የገባ ሲሆን፣ ለልዑኩ በሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። በሁለቱ አጎራባች ከተሞች መካከል ያለውን ታሪካዊ ወንድማማችነትና ማኅበራዊ መስተጋብር ይበልጥ ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር፣ የአመራሮች መቀራረብ ለሁለቱ ሕዝቦች አብሮነት ትልቅ ተምሳሌት መሆኑ ተገልጿል። የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩ መጠናከሩ፣ የፊታችን…

Read More

የአራት ዓመታት ተከታታይ ጥረት እና የሚጨበጥ ውጤት!

‎በዘንድሮው “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ላይ የሀገራዊ ርዕያችንን ተጨባጭ ስኬት መመልከት ትልቅ ክብር ነው። ውጤት ተኮር አመራራችን ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የኢንዱስትሪ መስፋፋት ተንጸባርቋል። ይኸውም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ በማድረግ፣ ባለፉት አራት አመታት ከ2,800 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የተቻለ ሲሆን፤ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዘጠኝ…

Read More

ቀፊራ፦ የታሪክና የዘመናዊነት ውህደት!

​የድሬዳዋ የንግድ ምልክት እና የታሪክ መዘክር የሆነው ታሪካዊው የቀፊራ የገበያ ማዕከል፣ በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ተገቢውን ትኩረት አግኝቶ በዘመናዊ መልኩ ታድሶ ዛሬ በይፋ ተመረቀ። ​ከ1939 ዓ.ም ጀምሮ የንግድና የባህል ማዕከል ሆኖ የቆየው ይህ ስፍራ፣ የነበረበትን የጽዳትና የትራፊክ መጨናነቅ ችግር በመቅረፍ ለከተማዋ አዲስ ድምቀት ሆኗል። ​ የማዕከሉ ጥንታዊ የህንጻ ጥበብ እና ታሪካዊ ቅስቶች (Arches) ሳይቀየሩ ጸንተው እንዲቆዩ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር በኮሪደር ልማት የታደሰውና ለበርካታ ሺህ ዜጎች የኑሮ መሰረት የሆነው ታሪካዊው የቀፊራ የገበያ ማዕከል በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል።

በ1939 ዓ.ም አሁን ያለውን ቅርፅ ይዞ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የቀፊራ የገበያ ማዕከል፣ ለዘመናት ሲታይበት የነበረውን የፅዳት ጉድለት፣ የትራፊክ መጨናነቅና ህገ-ወጥ ንግድ ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ በኮሪደር ልማት ታድሶ ለምረቃ በቅቷል። ማዕከሉ በዘመናዊ መልኩ መታደሱ ለሸማቾችና ለነጋዴዎች ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩ ባለፈ፣ ለከተማዋ ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል። የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ማዕከሉ…

Read More