በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የተመራ የአመራሮች ልዑካን ቡድን በሀረር ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት::
የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በማስመልከት የገፅታ ግንባታና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ለማጠናከር በሀረሪ ክልል እና በድሬዳዋ አስተዳደር በጋራ የተዘጋጀ የምርጫ ቅስቀሳና የወዳጅነት መርሃ-ግብር በሀረር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በመርሃ-ግብሩ የሚኖሩ ሁነቶችን እየተከታተለ የሚያደርሳችሁ ይሆናል!!


