የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ::

በመልዕክታቸውም ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሠላም፣ በአንድነትና በፍቅር አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በዓልን ደስተኛ ሆነው እንዲያሳልፉ ካለን ላይ በማካፈልና እርስ በእርስ በመረዳዳት እንዲሁም በመተሳሰብና በፍቅር በዓሉን ማሳለፍ እንደሚገባ ክቡር ከንቲባ በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል። በመጨረሻም በዓሉ የሠላም፣ የደስታ፣ የፍቅር እንዲሆን እምኛለሁ በማለት ክቡር ከንቲባው የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ::

የትንሣኤ በዓል በክርስቲያኖች ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው በዓል ነው። ሞት የተሻረበትና ሕይወት ዋስትና ያገኘበት ነው። ከሞት ባሻገር ሕይወት፣ ከመቃብር ባሻገር ትንሣኤ መኖሩ የታወጀበት ነው። ሞት መጨረሻ መቃብር መዳረሻ አለመሆናቸው የተረጋገጠበት ነው። በአዳም ምክንያት ወደ ምድር የወረደው ሰው፣ በክርስቶስ ምክንያት ወደላይ የወጣበት ነው። የዘንድሮውን ትንሣኤ የምናከብረው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሚያልፍ ፈተና ውስጥ እንዳለች እያሰብን ነው። መንገዳችን ረጅም፣…

Read More

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 62(9)እና በዐዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀፅ 2(ለ) መሠረት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደርን በርዕሰ መስተዳደርነት እንዲመሩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ በጸደቀው ደንብ ቁጥር 479/2013 አንቀጽ 4(2) እና የዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ባቀረቡት መሠረት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደን ለአንድ ዓመት ሹመታቸውን አራዝመዋል፡፡

Read More

የዓለም የነዳጅ ዋጋ መጠነ ሰፊ ቅናሽ አሳየ። የአንድ ድፍድፍ የነዳጅ ዋጋ በ13 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱ ተነገረ።

አሜሪካ እና ኢራን ሆርሙዝን ለመክፈት መስማማታቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። አሜሪካ እና ኢራን ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የኢራን መንግሥት ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ “ሁለትዮሽ የተኩስ አቁም” ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። በስምምነቱ መሰረትም ኢራን ለዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ዝግ አድርጋው የነበረውን የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ክፍት…

Read More

“መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ልዕልና አረጋግጧል”

በድሬዳዋ አስተዳደር ስምንተኛ ዓመትን የሚዘክር ደማቅ የህዝባዊ ድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል መጋቢት 24 ቀን የተጀመረውን ሀገራዊ የለውጥ ጉዞ ስምንተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ አስተዳደር ለገሀር አደባባይ ደማቅ የህዝባዊ ድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል። በመርሃ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ…

Read More

በቢዮ አዋሌ ክላስተር በሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች የተሰሩ የልማት ስራዎች ተጎበኙ።

” ኢትዮጲያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ” በሚል መሪ ሀሳብ የ 2018 ዓ.ም 7 ተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎችን የማስተዋወቅ መርሀ-ግብር በዛሬው እለት ቢቢዮ አዋሌ ክላስተር ተካሂዷል። በ 7 ተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎችን የማስተዋወቅ መርሀ-ግብር ከተካሄደ በኋላም በቢዮ አዋሌ ክላስተር በሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች የተሰሩ የልማት…

Read More

የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን በገጠር ያለውን ጥሬ ሃብት ወደ ኢንደስትሪ በመቀየር ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለፀ

የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር የገጠር ኢንደስትሪያላይዜሽን ሁሉን አቀፍ ልማት ስተራቴጂካዊ እምቅ አቅም ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር አካሄደ። በመርሃ ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባ አደም የገጠር ኢንደስትራላይዜሽን በገጠር ያለውን ሰፊ የሰው ሃይል ወደ ስራ የሚያስገባ፣ ለስራ ፍለጋ የሚደረገውን ፍልሰት የሚቀንስ፤ የተመጣጠነ የገቢ ዕድገት እንዲኖር የሚያስችል እንዲሁም…

Read More

ብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ በዋሂል ክላስተር ለሰባተኛ ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ተሳታፊ ዕጩዎቹን ለህዝብ አስተዋወቀ

ዕጩዎችን በመወከል በዋሂል ክላስተር ለተገኙ ታዳሚዎች ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ የድሬዳዋ አስተዳደር የካቢኔ አባልና የአስተዳደሩ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ነጻ ፣ ገለልተኛ እና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፓርቲያቸው ብልጽግና በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙሉካ በዋሂል ክላስተር የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ ተመልምለው የቀረቡ ዕጩዎች ቀደምሲል በምርጫ ቦርድ ከመመዝገባቸው…

Read More

በቃላድ ክላስተር የብልጽግና ፓርቲን ወክለው በ7ኛው ዙር ምርጫ የሚወዳደሩ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የሚተዋወቁበት መርሃ-ግብር ተካሄደ።

ይህ የብልጽግና ፓርቲ በድሬዳዋ አስተዳደር በቀለአድ ክላስተር የ7ኛው ዙር ምርጫ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ትውውቅ መድረክ የተዘጋጀው፣ ማህበረሰቡና ተወካዮቹ በደንብ እንዲተዋወቁና እንዲቀራረቡ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል። በመድረኩ ላይ በቃላድ ክላስተር የብልጽግና ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩ ዕጩዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባቶች፣ እናቶች፣ ወጣቶችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል። የቃላድ ክላስተር ነዋሪዎች ለእጩዎቹ ደማቅ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን፣ በምክር ቤት ድምፅ እንዲሆኑ…

Read More