የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በአስተዳደሩ ለሚገኙ ተቋማት ቢሮዎች የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ባለሞያዎች ዲጂታል ሚዲያ ለላቀ ተግባቦት በሚል መሪ ቃል በሐረር ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል
በየጊዜው እየዘመኑና ለአጠቃቀም ያላቸው ቅለትና ምቹነት በመላው አለም ሰፊ ተቀባይነትና ተወዳጅነትን በመቀዳጀት ዓለማቀፍ ገናን መደበኛ የሚዲያ ተቋማትን ሳይቀር ወደራሳቸው መሳብ የቻሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ያላቸውን ሰፊ የተደራሽነት ሽፋንና የተጽእኖ ፈጣሪነት አቅምን በመገንዘብ አብሮ መጓዝ የሚያስችል እውቀትና ክህሎት መጨበጥ ጊዜው የግድ የሚለው በመሆኑ ይህ ስልጠና መዘጋጀቱን ነው የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የመረጃ ማፍራት እና ማብቃት…


