ትንሿ #ኢትዮጵያ የሁላችን #ድሬዳዋ ታመሠግናለች።
በአስተዳደራችን አዘጋጅነት በውቧ የፍቅር ከተማችን ድሬዳዋ የተከበረው፤ የዘንድሮው 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና፣ ህዝቦች ቀን በዓል በሠላምና በስኬት በመጠናቀቁ ተደስቻለሁ እንኳን ደስ አላችሁ። ይህ ስኬት የበርካታ ህብረ-ብሔራዊ ኢትዮጵያዊያን ጥረትና ድካም ድምር ውጤት ነው። ለዚህ ታላቅ ስኬት ኀላፊነታችሁን የተወጣችሁ፤ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የድሬዳዋ ፖሊስና ትራፊክ አባላት፤ በጎ-ፈቃደኛ ወጣቶች፤ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች፤ የወጣት አደረጃጀቶች፤ በየደረጃው የምትገኙ የሴክተር…


