ግብፅና ሱዳን የህዳሴ ግድብን ለማስተጓጎል የያዙት አቋም ዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው- ምሁራን ::
ግብፅና ሱዳን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል የያዙት አቋም የዓለም አቀፍ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቀም ስምምነትን የጣሰ መሆኑን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የህግና ውሃ ሀብት ምርምር ምሁራን አስታወቁ። በግድቡ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ኢዜአ ካነጋገራቸው ምሁራን መካከል በዩኒቨርሲቲው የህግ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ጋድሰንድ ኮኖሮ÷የተባበሩት መንግስታት በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቀም ስምምነት ዙሪያ ያወጣው ህግ የተፋሰስ ሀገራት ፍትሐዊ…


