በድሬዳዋ አስተዳደር በተሻሻለው የመሬት ካሳ አዋጅ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ::

    ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ መንግስት በሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች ምክንያት የተፈናቀሉ ወይም ኑሮአቸው የተነካባቸው ሰዎች ሁሉ በመንግሥት በቂ እርዳታ ወይም ሌላ አካባቢ መዘዋወርን ጨምሮ ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ወይም ሌላ አማራጭ ማካካሻ የማግኘት መብት አላቸው ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባው ጽ/ቤት የልማት ተነሺዎች ካሳ ክፍያ፣ መልሶ መቋቋም እና ቀሬታ አፈታት አዲሱ አዋጅና ደንብ ዙሪያ…

    Read More

      የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በመንግስት ኮሙዪኒኬሽን ዘርፍ የቀጣይ 10 እና 5 አመታት መሪ እቅድ ላይ ከዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄዷል።

      በውይይቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በቀጣይ ቢሮው ከቀበሌዋችና ከሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት አብሮ የመስራቱን አጠናክሮ ከመቀጠል አንፃር፣ ባለፉት አመታት በዘርፉ የታዪ ችግሮችን ከመቅረፍ ፣የሴክተርና የቀበሌ የሰው ኃይል ማሟላትና የሚዲያና የኮሙዪኒኬሽን ዘርፍ መደበላለቅ ቢጠራ እንዲሁም የመልዕክተ ድሬ ጋዜጣ የቋንቋ ብዛህነት በኮሙዪኒኬሽን ዘርፍ ሊሻሻሉ ይገባል ሲሉ አንስተዋል። በተነሱት ሀሳቦች ላይ ምላሽ የሰጡት በአስተዳደሩ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ…

      Read More

        በድሬዳዋ አስተዳደር ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት በዛሬው እለት ተጀመረ፡፡

        በአለም ላይ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት ላለፉት 7 ወራት ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት በዛሬው እለትበ በ8 ኛ እና በ 12 ክፍል ተማሪዎች ተጀመረ፡፡ በዛሬው እለትም በአስተዳደሩ በሚገኙ የከተማና ገጠር ትምህርት ቤቶች ትምህርት ሲጀመር የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በየትምህርት ቤቶቹ ተዟዙረው ትምህርት ከማስጀመር በተጨማሪ ለተማሪዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ አበርክተዋል፡፡ በኮሮና ቨይረስ ምክንያት ተቋርጦ የቆየ…

        Read More

          Dugsiada dawlada ayaa dib loo bilaabi doonaa laga bilaaba maalinta isniinta ee fooda nagusoo haysa.

          Xafiiska waxbarashada ee ismaamulkan diri dhabe ayaa sheegay in uu so gaba gabaysmay u diyaar garawgi biaabida waxbarashada dugsiyada dawlada. Madaxa xafiiska waxbarashada ee ismaamulka marwo muluka maxamed ayaa shir jaraa`id oo ay warbaahinta siisay ayaay ku shaacisay in ay soo gaba gabaysantay diyaar garawgi loogu diyaar garoobayay in dib loo bilaabo waxbarashada sannadkani 2013…

          Read More

            የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባውን አካሄደ::

            አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን አካሄደ። በስብሰባው ላይ ባለፈው መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባደረጉት ንግግር ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ኢኮኖሚውበዋና ዋና ዘርፎች…

            Read More

              የበረሃ አንበጣ ጥቃት እንዳይስፋፋና የረሀብ አደጋ እንዳይከሰት ሥራዎች እየተሰሩ ነው -ጠ/ሚ ዐቢይ

              አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ የበረሃ አንበጣ ጥቃት እንዳይስፋፋና የረሀብ አደጋ እንዳይከሰት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል። ዘንድሮ ካጋጠመው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተጨማሪ አንበጣና ጎርፍ ተፈጥሯዊ ተግዳሮት መከሰቱን አውስተዋል። አንበጣ ከአንድ እስከ አምስት ደረጃዎች እንዳሉት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ደረጃ ሶስት የነበረውን…

              Read More

                ባለፈው በጀት አመት 6 ነጥብ 1 በመቶ ኢኮኖሚያዊ እድገት ተመዝግቧል – ጠ/ሚ ዐቢይ

                አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የ6 ነጥብ 1 በመቶ ኢኮኖሚያዊ እድገት መመዝገቡን ገለጹ፡፡ 5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያም ዓለም በኮሮና ቫይረስ…

                Read More

                  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ተመጀረ::

                  5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ተጀምሯል። ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው ስብሰባው እየተካሄደ ያለው። የመጀመሪያው አጀንዳ የምክር ቤቱን 6ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ያጸደቀ ሲሆን÷ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።

                  Read More

                    በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች ማህበር የምስጋና ፕሮግራም አካሄደ ።

                    በምስጋና ዝግጅቱ ላይ ከንቲባ አህመድ ቡህ እና አቶ እዝቅያስ ታፈሰን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸውና በቀድሞው ጊዜ ስመጥር የነበሩ መቶ የሚሆኑ ስፖርተኞችና መምህራን ተገኝተዋል። የኮረና ወረርሺኝ መከሰቱን ተከትሎ የቀድሞ የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች በነበረው አቶ ተካበ ዘውዴ አነሳሽነት እርስበርስ መደጋገፍን መነሻ ያደረገው በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች ማህበር በድሬዳዋ ለሚገኙ የአረጋውያን ድርጅቶች የተለያዩ ድጋፎችን ያደረገ…

                    Read More