ጎዳና የሚወጡ ልጆችን ትኩረት በመስጠት የበኩላችንን ግዴታ መወጣት እንዳለብን ተጠቆመ፡፡
በተለያዩ ሁኔታዎች ጎዳና የሚወጡ የህብረተሰቡ ክፍሎች በጎዳና ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለማቃለል የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን የሰራተኛና ማህበራዊ እና ሴቶችና ህጻናት ቢሮ በጋራ በመሆን ከpostive action for development (ፖሰቲቭ አክሽን ፎር ድቭሎፕመንት) ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በተለያዩ የሙያ ስልጠናዎች ያሰለጠናቸውን ታዳጊዎች አስመርቋል፡፡ በምርቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ…


