መስማት አለመቻል ብቁ አሽከርካሪ ከመሆን አያግድም !
የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መስማት የተሳናቸዉ ዜጎች የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ተጠቃሚ ለማድረግ በተዘጋጀዉ የአሰራር ማንዋል ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አካሄደ ፡፡ የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ቱሉ እንደተናገሩት የዚህ ማንዋል መዘጋጀት ዋና አላማ መስማት ለተሳናቸዉ ሰዎች የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል አሰራር ስርዓት በመዘርጋትና ተግባራዊ በማድረግ ተሸከርካሪን በማሽከርከር ከቦታ…


