በ 2017 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በ 5,550 ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች እንደሚሰሩ ተገለፀ::
”የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ሀሳብ የ 2017 ዓ.ም የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራዎች ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር በበአስተዳደሩ በአራቱም የገጠር ክላስተሮች መካሄድ ጀምሯል። በድሬዳዋ አስተዳደር ከለውጡ ማግስት ከተመዘገቡ በርካታ የለውጡ ስኬቶችና የህዝቡን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ ካደረጉ ስራዎች መካከል የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት በቀዳሚነት እንደሚጠቀስ በቢዮ አዋሌ ክላስተር በኬሀሎ ገጠር ቀበሌ ማስጀመሪያ መረሀ ግብሩን…


