“የ’World Without Hunger’ ጉባኤን ስናጠናቅቅ፣ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ውይይቶች የተሳኩ ይሆኑ ዘንድ አስተዋፅዖ ያበረከቱትን ተሳታፊዎች ከልብ አመሰግናለሁ።
አርባ ቢሊዮን ዛፎች በተተከሉበት ምርታማነትን በሚያሳድጉ የለውጥ ሥራዎች፣ ድርቅን በሚቋቋሙ አዝርዕት ልማት፣ በአረንጓዴዓሻራ መርሃ ግብር ሥራዎች አማካኝነት በዘላቂ የግብርና ሥራ የታየው የኢትዮጵያ ርምጃ በጉባኤው ቀርቧል። በ’ኢትዮዽያ ታምርት’፣ በአግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች ጥምር የሥራ ፈጠራ ሥራ፣ በገቢ እድገት እና ጽናት የታዩት ኢንቨስትመንቶች በአለም የግብርና ዘርፍ የኢትዮጵያን ሚና አጠናክረውታል። ረሃብን መዋጋት የጋራ ምላሽን ይሻል። ለዚህም ለምግብ ዋስትና የሚሆን…


