የተፈጥሮ ኃብትን በኃላፊነት የማልማት አይነተኛ ማሳያ የቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምዕራብ ወለጋ ዞን ገንጂ ወረዳ የሚገኘውን የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክትን ጉኝተዋል። በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ፕሮጀክቱ የተፈጥሮ ኃብታችንን ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት እንዴት ማዋል እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ መሆኑን ገልጸዋል። በመንግሥት እና በግል ኢንቨስተሮች ትብብር እየተከናወነ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር የአካባቢውን ማኅበረሰብ የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ በርካታ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጎበኙት የሃዋ ገላን አርሶ አደሮች ጽናትና የሙዝ እርሻ ስኬት::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቄለም ወለጋ ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ ተገኝተው በ”ሌማት ትሩፋት” መርሃ-ግብር የለማ የሙዝ እርሻን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል። አርሶ አደሮቹ መሬትና የውኃ ኃብትን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባህላዊ የመስኖ ዘዴዎችን በማቀናጀት አካባቢያቸውን ወደ ተስፋ ሰጪ የግብርና ማዕከልነት መለወጣቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ተመልክተዋል። በተለይም የመንገድ መሠረተ ልማት መገንባት የአርሶ አደሩን ምርት በቀላሉ ወደ ገበያ ለማድረስ…

Read More

የቄጦ የመስኖ ፕሮጀክት፤ ለሰዲ ጫንቃ እና ሃዋ ገላን ወረዳዎች አዲስ የልማት ተስፋ::

ለሰዲ ጫንቃ እና ሃዋ ገላን ወረዳዎች ትርጉም ያለው ለውጥ እያመጣ የሚገኘው የቄጦ የመስኖ መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ለግብርናው ዘርፍ አዲስ ገጽታ እየፈጠረ ይገኛል። ፕሮጀክቱ የአካባቢውን የተፈጥሮ መልክዓ-ምድር በአግባቡ በመጠቀም፣ ለግብርና ሥራ የማይቋረጥ የውኃ አቅርቦት እንዲኖር ታስቦ የተተገበረ ነው። በአሁኑ ወቅትም የመስኖ ሥራውን በቀጥታ ጥቅም ላይ በማዋል የታረሰ እና የለማ መሬት ለኅብረተሰቡ ጉልህ ፋይዳ ማስገኘት ጀምሯል። ከመስኖው…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ረጀብ ጣይፕ ኤርዶዋን በ9ኛው የቱርክ-ኢትዮጵያ የጋራ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ስምምነት ሰነድ እንዲሁም በኢነርጂ ዘርፍ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

እነዚህ ስምምነቶች በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል እየተጠናከረ የመጣውን አጋርነት ይበልጥ የሚያጎለብቱ ሲሆን፤ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሰረቱ መስኮች፤ ያላቸውን የሥራ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አመላካች ነው።‎

Read More

የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫው ፅ/ቤት የ 7 ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ” የስንዴ ነዶን ” ለአባላቱ ይፋ አደረገ።

” ኢትዮጲያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ” በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ የ 7 ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ” የስንዴ ነዶን ” ይፋ ማድረጊያ መርሀ-ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር በዛሬው እለት ሲካሄድ … በምስል …።

Read More

” ኢትዮጲያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ” በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ የ 7 ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶ እና ምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መርሀ-ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር በአሁን ሰአት እየተካሄደ ይገኛል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮም በመርሀ-ግብሩ ላይ ያሉትን አጠቃላይ መረጃዎች ወደ እናንተ የምናደርስም ይሆናል።

Read More

“ድሬዳዋ የነፃ ንግድ ቀጠና እና የምስራቁ የሀገራችን ኢንዱስትሪ መዕከል ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የእድገት ግስጋሴዋን የሚመጥን የውሃና ሳንቴሽን አገልግሎት በእጅጉ ያስፈልጋታል”:- የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር

በድሬዳዋ አስተዳደር ከአንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን( 1. 3 ቢሊዮን) ብር በላይ በሆነ ወጭ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ፣ ማጣሪያና ማስወገጃ የኦፕሬሽንና ጥገና ፕሮጀክት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል። በዚህም በመርሃ-ግብሩ የተገኙት ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር የግንባታ ፕሮጀክቱ የአስተዳደሩን የፍሳሽ አያያዝና አወጋገድ ስርዓትን በላቀ ደረጃ የሚያሻሽል መሆኑን ተናግረው፤ ድሬዳዋ የነፃ ንግድ ቀጠና እና የምስራቁ የሀገራችን ኢንዱስትሪ መዓከል ከመሆኗ ጋር…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ::

የ2018 ዓ/ም የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር በአስተዳደሩ የወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን አስተባባሪነት በበጎ ፈቃድ ተግባራቶች የላቀ ተሳትፎ ለነበራቸው ግለሰቦች፣ባለሀብቶች ፣ ግብረሰናይ ድርጅቶች፣የወጣትና ሴቶች አደረጃጀቶች የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል ። በመርሃ ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ተገኝተው በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጽት፤ ወጣቶች ለሀገሪቱ ብሎም ለአስተዳደሩ በማህበራዊ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገነባውን ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት ለማስጀመር የውኃ እና ኢነርጂ ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ድሬዳዋ ከተማ ገብተዋል።

ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ በክቡር አብዲ ሙክታር፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ም/አፈጉባኤ በክብርት ከሪማ አሊ፣ በካቢኔ አባላት እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Read More