ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር ጋር ተወያዩ::
በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በዛሬው ሁለተኛ ቀን ውሎው በተለያዩ ወሳኝ አህጉራዊ አጀንዳዎች ላይ ምክክሩን ቀጥሏል። በጉባኤው ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ማያርዲት ጋር ተገናኝተው መክረዋል። መሪዎቹ በውይይታቸው በቀጣናዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ አተኩረዋል።


