የኮሪደር ልማትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሡት ሐሳብ

****************** የኮሪደር ልማት የቦታና ጊዜ ምልከታን የሚቀይር ነው። ለአብነትም በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ ሺህ በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ተገንብቷል። በርካታ ወጣቶች ወደ ስፖርት እየተመለሱ ነው። ይህም ማህበረሰብን የመገንባት ስራ ነው። የትውልድ ስነ ልቦና ስብራትን እያረቀ ያለ ስራም ጭምር ነው። ይህን ማንም ሰው የሚያየው፤ ማንም ሰው የሚናገረው ጉዳይ ነው።

Read More

የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክትን በ24 ወራት ውስጥ አጠናቅቀን እንጨርሳለን

******** ልክ እንደተፈጥሮ ጋዝ ሁሉ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የድፍድፍ ነዳጅ ክምችት እንዳለ በሶስተኛ ወገን መረጋገጡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ነዳጅ ማጣሪያውንም በ24 ወራት ውስጥ አጠናቅቀን እንጨርሳለን ብለዋል። የጋዝና ነዳጅ ሥራ ከውጭ የሚገባውን ኃይል በመተካት የወጪ ምንዛሬ ለመቆጠብ ይረዳናል ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለነዳጅና ለማዳበሪያ ከፍተኛ ሃብት ታወጣለች፤ ይህን ማስቀረት ከቻልን ብዙ ሃብት ለመቆጠብ ያስችላል ብለዋል።…

Read More

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል። በመደበኛ ስብሰባው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ምላሽ እና…

Read More

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ጥቅምት 18 ቀን፣ 2018 ዓ.ም፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በመወያየት የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽን ያጸድቃል::

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

Read More

የምስራቅ ኢትዮጵያ ጥምር የፀጥታ ሀይል ባካሄደው የጋራ ስምሪት እና በወሰደው ጠንካራ እርምጃ የሽብርተኛው የሸኔ ቡድን አባላትን በመደምሰስ እና በመማረክ ቡድኑ ይንቀሳቀስባቸው የነበሩ አካባቢዎችን ነፃ በማውጣት ወደ አስተማማኝ ሰላም መመለስ መቻሉ ተገለፀ።

በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ፤ የምስራቅ ኢትዮጵያ ጥምር የጸጥታ ሀይልን በመወከል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የምስራቅ ኢትዮጵያ ጥምር የፀጥታ ሀይል ባካሄደው የጋራ ስምሪት እና በወሰደው ጠንካራ እርምጃ 43 የጠላት ሀይል መደምሰሳቸውን የገለፁ ሲሆን “ጃል ሐረርጌ” የተሰኘው የቡድኑ መሪ ከተደመሰሱት መሀከል መኖሩን እና ጃል ቦባሳ የተሰኘ የቡድኑ ምክትል መሪ ደግሞ በውጊያ…

Read More

የታንዛንያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታዲየም ለማረግ ማምሻውን ድሬዳዋ ከተማ ገብቷል

ብሄራዊ ቡድኑ የፊታችን ማክሰኞ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል። ብሄራዊ ቡድኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ካሊድ መሀመድ እንዲሁም በካቢኔ አባላትና በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

Read More

የዳዊት ለአረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከሉ ያስገነባው የአረጋውያን ባለ አንድ ወለል ህንፃ ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ

የዳዊት ለአረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከሉ ያስገነባው የአረጋውያን ባለ አንድ ወለል ህንፃ ግንባታ ተጠናቆ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመረቀ። የዳዊት ለአረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር በ1998 ከተመሰረተ ጊዜ አንስቶ ደጋፊና ጧሪ የሌላቸውን ችግረኛ አረጋዊያንን እያገለገለ የሚገኝ በጎ አድራጎት ማህበር ነዉ ። ማህበሩ ይህንን በጎ ተግባሩን በማስፋትና በማሳደግ በ2006 ዓ.ም በድሬዳዋ አስተዳደር በተሰጠው ከሊዝ ነፃ…

Read More

/”ከዚህ በኋላ ተኝቼ ነው የማድረው እንቅልፍ አልባ ለሊቶቼ አብቅተዋል”

በድሬዳዋ አስተዳደር የቤት ግንባታ የተከናወነላቸው አቅመ ደካማ ወገኖች በድሬዳዋ አስተዳደር በዛሬው ዕለት በክረምት በጎ ፍቃድ በወረዳ 05፣ 08 እና 02 የተገነቡ ከ14 በላይ የሚሆኑ ቤቶች በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እና በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ በክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ ተመርቀዋል። በዚህም የቤት ግንባታ ከተደረገላቸው አቅመ ደካማ ወገኖች መካከል የሁለት ልጆች…

Read More

“በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች የአቅመ ደካማ ወገኖችን ችግር በተጨባጭ የቀረፉ አበረታች ስራዎች ተከናውነዋል”-

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በክረምት በጎ ፍቃድ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ በወረዳ 05፣ 08 እና 02 የተገነቡ ከ14 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን መርቀው ቁልፉን ለባለቤቶቹ አስረክበዋል። በአስተዳደሩ በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች የአቅመ ደካማ ወገኖችን ችግር በተጨባጭ የቀረፉ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ምክትል…

Read More