በመደመር መፅሀፍ ሽያጭ ድሬዳዋ ከተማ ላይ የተሰራው እምርታ ቤተ-መፅሀፍ ለነዋሪዎች የንባብ ባህል መዳበር ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ
በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በተፃፈው በመደመር ትውልድ መፅሀፍ ሽያጭ እንዲሁም በአስተዳደሩ ድጋፍ ዘመናዊና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባው እመርታ ቤተ-መፅሀፍ አሁን ላይ የግንባታ ሂደቱ እንደተጠናቀቀና በቅርቡ ተመርቆም ለነዋሪዎች ክፍት እንደሚሆንም የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንደሰን አባይ ተናግረዋል። ቤተ-መፅሀፉ በአንድ ጊዜ አንድ ሺ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን ማስተናገድ እንደሚችል የጠቆሙት አቶ ወንደሰን አገልግሎት መስጠት ሲጀምርም…


