ድሬዳዋን የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ ተችሏል:-ከንቲባ ከድር ጁሀር
ህዝባዊ የውይይት መድረክ በድሬዳዋ አስተዳደር እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ሠላምና ፀጥታን በማረጋገጥ ድሬዳዋን ከምትታወቅበት በተጨማሪ የኮንፍረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ እንደተቻለ ገልፀዋል። የከተማዋን ታሪክና ደረጃ የሚመጥኑ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች እና ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሚገኙም አመላክተዋል። ከህዝቡ ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል::


