የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በአስተዳደሩ ከሚገኙ ምሁራን ጋር በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም እና በምሁራን ሁለንተናዊ ሚና ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ ::
ለድሬዳዋ አስተዳደር ምሁራን እና ከፍተኛ የመንግስት ባለሙያዎች የተዘጋጀው የምክክር መድረክ በድሬዳዋ ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ የብልጽግና አለማቀፋዊ ትርጉምና አሌመንቶች አገራት በብልጽግና እንዴት ይለካሉ፣ የብልጽግና ፓርቲ ዋና አላማዎች እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራሞች አላማን መሰረት ያደረገ የምክክር መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። መድረኩ በሁለት ክፍል የተዘጋጀ ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል ስለ ብልጽግና መሰረታዊያን ማለትም ስለ ብልጽግና ቃል አመጣጥና…


