ድሬዳዋ እና የፈረንሳይ ሌጉ ከተማ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር በማጠናከር በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ
የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በፈረንሳይ ሌጉ ከተማ ከንቲባ ሊዮኒዳስ ሰርጅ ከተመራ ልኡካን ቡድን ጋር የሁለቱን ከተሞች እህትማማችነት ለማጠናከር እና በቀጣይ በጋራ አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ተወያይተዋል። በውይይቱም ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ለእንግዶች የእንኳን ደና መጣችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ በኢትዮጲያ እና በፈረንሳይ መካከል ጠንካራ ወዳጅነት እና ትብብር መኖሩን ገልፀዋል። ምክትል…


