ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚያስታውሱና የሚዘክሩ የተለያዩ መርሀ-ግብሮች በድሬዳዋ አስተዳደር ተካሄደ ።
አሸባሪው የህወሃት ቡድን ጥቅምት 24 \ 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚዘክሩ የተለያዩ መርሃ-ግብሮች በድሬዳዋ አስተዳደር ተካሂደዋል ። በመርሀ ግብሮቹ ላይም ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚያስታውሱና የሚዘክሩ ስራዎች ከመቅረባቸውም ባለፈ የጧፍ ማብራት ስነ-ስርአትም ተካሂዷል ። በዚሁም መርሀ-ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለአገርም ሆነ ለህዝብ ግድ የሌለውና ኢትዮጵያን…


