የእየሱስ ክርስቶስ ልደት(የገና)በዓል ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ለማስቻል ፖሊስ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ገለፀ ፡፡
በዓሉን በማስመልከት የድሬዳዋ ፖሊስ የህ/ግንኙነት ዋና ክፍል ሀላፊ ም/ኢ/ር ባንታለም ግርማ ለተለያዩ የሚድያ አካላት መግለጫ ሰተዋል። ሃላፊው በመግለጫቸው በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ታላላቅ በአላት መካከል እንደ የእየሱስ ከርስቶስ ልደት (የገና) በአል እንደመሆኑ ለበአሉ ፍፁም ሰላማዊነት የድሬዳዋ ፖሊስ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ነው የገለፁት ፡፡ ም/ኢ/ር ባንታለም ግርማ እንዳስታወቁት በእዚሁ በዓል ምንም አይነት የወንጀል…


