በነገው ዕለት በድሬዳዋ ለሚቀጥለው ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሁሉም ዘርፍ ዝግጅት መጠናቀቁን የድሬዳዋ አስተዳደርና የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ
ለቤቲንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ የመጡ የእግር ኳስ ቤተሰቦች በሙሉ ፍቅር ወደሆነችው ከተማችን ድሬዳዋ እንኳን በሰላም መጣችሁ ብለዋል ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳርን በመወከል ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ የለውጡ አመራር በሁሉም ዘርፍ ድሬዳዋን ወደ ቀድሞ ከፍታዋ ለመመለስ በተያዘው አቅጣጫ በልዩ ትኩረት የውድድሩን በመመራቱ ዝግጀቱ መጠናቀቁን አሳውቀዋል ፡፡ ቤተኪንግ ኢትዮጵያ…


