በድሬዳዋ የጥምቀት እና ከተራ በዓል በደማቅ ሁኔታ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ መከበሩን ፖሊስ ገለፀ::
የድሬደዋ ፖሊስ እንዳስታወቀው በሀይማኖታዊ ስርአቱ መሰረት ሁሉም ታቦታት በዝምሬና ምስጋና በሰላም ወደ የደብራቸው በሰላም መግባታቸውን ገልፆ ለበዓሉ ፍፁም ሰላማዊነት ምስጋናውን አቅርቧል:: ከጥምቀትና ከተራ በአል አከባበር ጋር ተያይዞ ለበአሉ ፍፁም ሰላማዊነት አስቀድሞ የበአል የፀጥታ እቅድ በማውጣት ወደ ስራ መግባቱን የገለፀው ፖሊስ በጥምቀት ሆነ ከተራ በአል ምንም አይነት የፀጥታ ችግርም ሆነ የወንጀል ተግባራት ሳይፈፀሙ እንዲሁም የትራፊክ አደጋ…


