ሴቶችን በስራ ቦታቸው ላይ ብቁ ውጤታማ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የመደገፍ እና ወደ አመራርነት የማምጣት ስራን ትኩረት ሰቶ እየሰራ እንደሚገኝ የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ ባለስልጣን አስታወቀ
በባለስልጣኑ አለም አቀፉ የሴቶች ቀን ማርች 8 “ሴቶችን እናብቃ ፤ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሀግብሮች ተከብሯል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ በኢትዮጵያ ለ48ኛ ግዜ የሚከበረው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአስተዳደራችን በተለያዩ መርሀግብሮች እየተከበረ ሲገኝ በድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ ባለስልጣን የሚገኙ ሰራተኞችም እለቱን በተለያዩ መርሀግብሮች አክብረውታል። በዚሁ መርሀግብር መክፈቻ ላይ የተቋሙን ሀላፊ በመወከል…


