ኢትዮጵያ በቀጠናው በኢነርጂ እና አቪዬሽን ዘርፍ ትብብር እንዲኖር አበክራ እየሰራች ነው፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ኢትዮጵያ በቀጠናው በኢነርጂ እና አቪዬሽን ዘርፍ ትብብር ብሎም ትስስር እንዲኖር አበክራ እየሰራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ሀገሪቱ ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ዕምቅ አቅም እንዳላት ገልፀዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኬኒያ እና ታንዛኒያ ጉብኝት በአቪዬሽን እና ኢነርጂ ዘርፍ አካባቢያዊ ትስስር እንዲኖር ለማድረግ ያለመ መሆኑን…


