#ዜና | በህብረተሰቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ የህዝብ ተመራጭ አባላት ገለጹ፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ የህዝብ ተመራጭ አባላቶች ከተለያዩ ወረዳዎች ከተወከሉ ህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ አስተዳደር የህዝብ ተመራጭ አባል የሆኑት ዶክተር ቢፍቱ መሀመድና አቶ አብዱልጁሀድ መሀመድ ከተለያዩ ወረዳዎች ከተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአስተዳደሩና በፌደራል ደረጃ ሊፈቱ የሚገቡ የህዝቡ የልማት፣ የኑሮ ማሻሻያ እና አንገብጋቢ የሆኑ መሠረታዊ ጥያቄዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡…


