በሀገሪቱ እየተመዘገቡ ያሉ የልማት ግቦች የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያበስሩ ናቸው” የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር።
ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ይህን ያሉት በትላንትናው እለት ከሰዓት በኋላ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነዉ ። በውይይቱም በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ እና በሳቸው አመራር ሰጪነት የሚመራው የለውጥ ሀይል የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልጽግና ከማረጋገጥ አንጻር ያስቀመጧቸውን ግቦች በተጨባጭ ተግባራዊ እየሆኑ ና የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያበስሩ…


