300 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ያለው የቻይና ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ
300 ሚሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ያለው ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ ኩባንያ፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ወረቀት የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኩባንያውን አመራሮች በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። የኩባንያው አመራሮች ስለ ኢንቨስትመንት ዕቅዳቸው ዝርዝር መረጃዎችን ማቅረባቸው ተጠቅሷል። የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ፤ በኮርፖሬሽኑ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ማዕከሎችን፤ማበረታቻዎችን እንዲሁም የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥን…


