ድሬዳዋን ዘመናዊና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የኮሪደር ልማት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለፀ
በዛሬው ዕለት የኮሪደር ልማት ድሬዳዋ ላይ ተግባራዊ በሚደረግበት ነጥቦች ዙሩያ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በተገኙበት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል። የኮሪደር ልማት በተለያዩ አዋጅችና ደንቦች የተቀመጠ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች እንዳልተተገበረ ምክትል ከንቲባው አንስተው፤ የኮሪደር ልማት ድሬዳዋን ለማዘመን ብሎም ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል። በመድረኩ በድሬደዋ አስተዳደር የተመረጡ የከተማ…


